የሀገር ውስጥ ዜና

በፓራሊምፒክ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑክ በፓሪስ አቀባበል ተደረገለት

By Feven Bishaw

August 26, 2024

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለ17ኛው የፓሪስ 2024 ፓራሊምፒክ ተሳታፊ የኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን ደማቅ አቀባበል ተደረገለት።

የ33ኛው የፓሪስ ኦሊምፒክ ውድድር አካል የሆነው 17ኛው የፓራሊምፒክ ውድድር በፈረንጆቹ ከነሐሴ 28 እስከ መስከረም 8 ቀን 2024 ይካሄዳል፡፡

ኢትዮጵያን ወክሎ የሚሳተፈው ልዑክም ፓሪስ ሲደርስ በፈረንሳይ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሀገሪቱ ከሚኖሩ የዳያስፖራ አባላት ጋር በመሆን ልዩ አቀባበል አድርገውለታል፡፡

በፓራሊምፒክ ውድድሩ ኢትዮጵያ በሁለቱም ጾታ እንደምትሳተፍ የኤምባሲው መረጃ አመላክቷል፡፡