Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአማራ ክልል ከ150 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በሩዝ ሰብል ተሸፈነ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በ2016/17 የመኽር ምርት ዘመን ከ150 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በሩዝ ሰብል መሸፈኑ ተገለፀ።

በክልሉ በምግብ ራስን ለመቻል በሚደረገው ጥረት የሩዝ ሰብልን በሚታረስ መሬት በማስፋፋት እና ምርታማነቱን በማሳደግ ረገድ በሰፊው እየተሠራ እንደሚገኝ ተመላክቷል፡፡

ለሩዝ ምርት እምቅ አቅም ያላቸውንና ከአሁን በፊት በሩዝ ምርት የማይታወቁ አካባቢዎችን በመለየት ወደ ተግባር በማስገባት አበረታች ውጤት መመዝገቡም ተገልጿል፡፡

በክልሉ በ2016/17 የመኽር ምርት ዘመን ከ150 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በሩዝ ሰብል መሸፈኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ መረጃ ያመላክታል።

ምርታማነቱን ለማሳደግም የቴክኖሎጂና የግብዓት አቅርቦት በወቅቱ ለአርሶ አደሩ ተደራሽ ለማድረግ ጥረት መደረጉ የተገለፀ ሲሆን ÷በዚህም በሄክታር 53 ኩንታል ምርት ይሰበሰባል ተብሎ ይጠበቃል ነው የተባለው።

Exit mobile version