አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በስዊዘርላንድ በተካሄደው በሉዛን ዳይመንድ ሊግ በ1 ሺህ 500 ሴቶች ውድድር ፣በ3ሺህ ሜትር ወንዶችና በ3ሺህ ሜትር ወንዶች መሰናክል ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸንፈዋል፡፡
አትሌት ድሪቤ ወልተጂ የ1 ሺህ 500 የሴቶች ውድድርን ቀዳሚ ሆና በመግባት ስታሸንፍ ፍሬወይኒ ሀይሉ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቅቃለች፡፡
አትሌት ድሪቤ ከትናንት በስቲያ በተካሄደው የሉዛን ዳይመንድ ሊግ የ3 ሺህ ሜትር ሴቶች ውድድር የቦታውን አዲስ ሪከርድ በማስመዝገብ ማሸነፏ ይታወሳል፡፡
በተመሳሳይ በ3ሺህ ሜትር ወንዶች ውድድር አትሌት በሪሁ አረጋዊ ሁለተኛ፣ዮሚፍ ቀጀልቻ ሶስተኛ በመሆን ውድድሩን ሲያጠናቅቁ በ3ሺህ ሜትር ወንዶች መሰናክል ደግሞ ሳሙኤል ፍሬው ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቋል፡፡