አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ታምራት ቶላ በትውልድ አካባቢው ላሉ ችግረኛ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ መግዣና ለታዳጊዎች ስፖርት ማጠናከሪያ የሚሆን የ1 ሚሊየን ብር ስጦታ አበርክቷል፡፡
አትሌቱ ዛሬ በትውልድ አካባቢው ኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አሌልቱ ወረዳ ሚአዋ ከተማ አቀባበል ተደርጎለታል፡፡
በዚህ ወቅትም ለችግረኛ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ መግዣና ለታዳጊዎች ስፖርት ማጠናከሪያ የሚሆን የ1 ሚሊየን ብር ስጦታ አበርክቷል፡፡
በቀጣይም አንድ ትምህርት ቤት ገንብቶ ለማስረከብ ቃል የገባ ሲሆን÷ በሚአዋ ከተማ እየገነባ ያለው ባለ አምስት ወለል ሆቴል በመጠናቀቅ ላይ መሆኑን ጠቁሞ በቀጣይ ለአካባቢው ወጣቶች የስራ እድል እደሚፈጥር ገልጿል፡፡
የአሌልቱ ወረዳ አስተዳደር በበኩሉ ለአትሌቱ የወርቅ ሀብል አበርክቶለታል፡፡
በአበበ የሸዋልዑል