ስፓርት

የፕሪሚየር ሊጉ ሁለተኛ ሳምንት ሶስት ጨዋታዎች ዛሬ ይደረጋሉ

By Mikias Ayele

August 25, 2024

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ ሲቀጥሉ ቼልሲ ከዎልቨርሃምተን ወንደረርስ እንዲሁም ሊቨርፑል ከብረንትፎርድ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

ቼልሲ ከዎልቨርሃምተን ወንደረርስ የሚያደርጉት ጨዋታ ቀን 10 ሰዓት ላይ ሲደረግ ሁለቱ ቡድኖች በጨዋታው የመጀመሪያ ጎል እና ነጥብ ይዞ ለመውጣት ወደ ሜዳ ይገባሉ፡፡

በፕሪሚየር ሊጉ የመጀመሪያ ሳምንት ዎልቨርሃምተን ወንደረርስ በአርሰናል እንዲሁም ቼልሲ በማንቼስተር ሲቲ በተመሳሳይ 2 ለ 0 የተሸነፉ ሲሆን ሁለቱ ቡድኖች እስካሁን ጎል ማስቆጠር አልቻሉም፡፡

በጨዋታው አዲስ የቼልሲ ፈራሚ ፔድሮ ኔቶ የቀድሞው ክለቡን በተቃራኒ የሚገጥም ይሆናል፡፡

በተመሳሳይ ቀን 10 ሰዓት ቦርንማውዝ ከኒውካስትል የሚያደርጉት ጨዋታም ተጠባቂ ነው፡፡

ምሽት 12፡30 ላይ ደግሞ ሊቨርፑል ብረንትፎርድን በአንፊልድ ያስተናግዳል፡፡

ሁለቱ ቡድኖች ፕሪሚየር ሊጉን በድል የጀመሩ ሲሆን ሊቨርፑል ኢፕስዊች ታውንን ብረንትፎርድ ክሪስታል ፓላስን ማሸነፋቸው የሚታወስ ነው፡፡