የሀገር ውስጥ ዜና

የኅዳሴ ግድብ 3ኛ እና 4ኛ ተርባይኖች ሥራ ጀመሩ

By amele Demisew

August 25, 2024

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ በትናትናው ዕለት 3ኛ እና 4ኛ ተርባይኖች ሥራ መጀመራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አበሰሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ የኅዳሴ ግድባችን በትናንትናው ዕለት 3ኛው እና 4ኛውን ተርባይኖች ሥራ አስጀመርን ብለዋል።

ሌሎቹ ዩኒቶች በተቀመጠላቸው እቅድ መሰረት በመከናወን ላይ ይገኛሉ ሲሉም ገልጸዋል።