አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ሣምንት ጨዋታዎች ቶተንሃም ሆትስፐር፣ ዌስትሃም፣ ኖቲንግሃም ፎረስት፣ ፉልሃም እና ማንቼስተር ሲቲ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡
በዚህም መሠረት÷ ቶተንሃም ኤቨርተንን 4 ለ 0፣ ዌስትሃም ክሪስታል ፓላስን 2 ለ 0፣ ኖቲንግሃም ፎረስት ሳውዝ ሃምተንን 1 ለ 0፣ ፉልሃም ሌስተር ሲቲን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል፡፡
ኢፕስዊች ታውንን ያስተናገደው ማንቼስተር ሲቲ ደግሞ 4 ለ 1 በመርታት በፕሪሚየር ሊጉ ሁለተኛ ድሉን አስመዝግቧል፡፡
በዚሁ ጨዋታ የውኃ ሰማያዊዮቹ የፊት መሥመር ተጫዋች ኤርሊንግ ሃላንድ ሦስት ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል፡፡
ዛሬ ቀን ላይ በተደረገ የሁለተኛ ሣምንት ጨዋታ ማንቼስተር ዩናይትድ በብራይተን 2 ለ 1 መሸነፉ ይታወቃል፡፡
የሁለተኛ ሣምንት የጨዋታ መርሐ-ግብር ሲቀጥል ምሽት 1 ሠዓት ከ30 ላይ አስቶንቪላ ከአርሰናል ይገናኛሉ፡፡