አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፈረንጆቹ ከነሐሴ 27 እስከ 31 ቀን በፔሩ ሊማ ለሚካሄደው የዓለም ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ልዑክ ወደ ፔሩ አቅንቷል።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር አትሌት ደራርቱ ቱሉና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ እንግዳ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለልዑካን ቡድኑ አባላት አሸኛኘት አድርገውላቸዋል።