አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አንድነታችን አጽንተን በጋራ ችግኞችን በመትከል ኢትዮጵያን በልማት እንገነባለን ሲሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው ገለጹ፡፡
የአንድ ጀንበር አረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች እየተከናወነ ይገኛል፡፡
አቶ እንዳሻው ጣሰው ÷ መርሐ ግብሩ ድህነትን የምናሸንፍበት እና የአየር ንብረት ለውጥን ተከትሎ የሚመጣ ቀውስን የምንከላከልበት ነው ብለዋል፡፡
የችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ አንድነታችን አጽንተን በጋራ ችግኞችን በመትከል ኢትዮጵያን በልማት ለመገንባት እድል የፈጠረ መሆኑንም አንስተዋል፡፡
በመርሐ ግብሩ የክልሉን ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ጨምሮ በርካታ ቁጥር ያላቸው የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ያለምንም ልዩነት እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡
በኤፍሬም ምትኩ፣ ይስማው አደራውና መሳፍንት እያዩ