Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሩሲያና ዩክሬንን ለማሸማገል ኪዬቭ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ከመከሩ ከሣምንት በኋላ ከዩክሬን ፕሬዚዳንት ጋር ለመወያየት ኪዬቭ ገብተዋል፡፡

በዩክሬን እና ሩሲያ መካከል ያለው ጦርነት እንዲቆምና ሰላም እንዲሰፍን ሕንድ ጥሪ ስታቀርብ መቆየቷ ይታወሳል፡፡

የዩክሬን እና የመካከለኛው ምሥራቅ ግጭቶችን በመጥቀስ፤ በጦርነት የሚፈታ ችግር አለመኖሩን ወደ ኪዬቭ ከማቅናታቸው በፊት በሰጡት መግለጫ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

በዚሁ ወቅትም ሕንድ በሀገራቱ መካከል ሰላም እንዲሰፍን ውይይትን ትደግፋለች፤ ለዚህም ከወዳጅ ሀገራት ጋር በመሆን አስፈላጊውን ድጋፍ ታደርጋለች ማለታቸውን ሲ ኤን ኤን ዘግቧል፡፡

Exit mobile version