አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ- ግብር እስካሁን 157 ሚሊየን ችግኝ መተከሉን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።
በአረንጓዴ አሻራ የአንድ ጀምበር 600 ሚሊየን ችግኞችን የመትከል መርሐ ግብር በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች እየተካሄደ ይገኛል።
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴዔታ ሰላማዊት ካሳ መርሐ ግብሩን አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም÷ በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እስካሁን 157 ሚሊየን ችግኝ መተከሉን ገልጸዋል።
አዲስ አበባ የሚገኘው የሁኔታዎች መከታተያና የመረጃ ማደራጃ ማዕከል የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላን አስመልክቶ ያሉ መረጃዎችን እንደሚያደርስም መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡