አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብርን አጠናክረን መቀጠል ከቻልን ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ልማት ለዓለም ተምሳሌት ትሆናለች ሲሉ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አለሚቱ ኡሞድ ገለጹ።
በጋምቤላ ክልል የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እየተከናወነ ነወ።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አለሚቱ ኡሞድና የክልል፣ የዞንና የወረዳ አመራሮችን ጨምሮ መላው ነዋሪዎች በችግኝ ተከላው ተሳትፈዋል።
ርዕሰ መስተዳድሯ ፥ በክልሉ በጎደሬ ወረዳ ጎሽኒ ቀበሌ ተገኝተው እንደገለፁት ÷ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብርን አጠናክረን መቀጠል ከቻልን ኢትዮጽያ በአረንጓዴ ልማት ለዓለም ተምሳሌት ትሆናለች ብለዋል።
በዛሬው እለት እየተከናወነ በሚገኘው የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር ላይ መላው ሕዝብ መሳተፍ ይጠበቅበታል ማለታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
በመሆኑም እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት ድረስ አመራርሩና ሕዝቡ በመቀናጀት አሻራችንን እናስቀምጣለን ብለዋል።