አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አወል አርባ በዛሬው የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ሀገርና ትውልድን የሚያኮራ ተግባር እንፈጽማለን አሉ፡፡
በሀገር አቀፍ ደረጃ በአንድ ጀምበር 600 ሚሊየን ችግኞችን የመትከል መርሐ-ግብር አካል የሆነ የአረንጓ ዐሻራ ማኖር መርሐ-ግብር በአፋር ክልል እየተካሄደ ነው፡፡
በዚሁ ወቅትም ርዕሰ መሥተዳድሩ ባደረጉት ንግግር÷ አረንጓዴ ዐሻራ ዝናብ አጠር ለሆነው የአፋር አካባቢና ለአርብቶ አደሩ ማሕበረሰብ ትልቅ ፋይዳ ስላለው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡