አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አረንጓዴ፣ ውብና ምቹ ኢትዮጵያን ገንብተን ለመጪው ትውልድ እናስረክባለን ሲሉ የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽሕፈት ቤት የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) ገለጹ።
ዛሬ የአንድ ጀምበር የ600 ሚሊየን የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ከማለዳው ጀምሮ በመላ አገሪቱ ተጀምሯል።
በዚሁ ታሪካዊ እለትም የብልፅግና ፓርቲ የዋናው ጽህፈት ቤት አመራሮች ከመዲናዋ ነዋሪዎች ጋር በመሆን የአረንጓዴ አሻራቸውን እያኖሩ ነው።
የፓርቲው የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) የአንድ ጀምበር የ600 ሚሊየን ችግኞች ተከላን እናሳካለን ብለዋል።
ችግኝ መትከል ብቻውን በቂ አይደለም ፤ችግኝ በመንከባከብ ለደን ልማት፣ ለግብርና፣ ለቱሪዝምና ሌሎች መስኮች ትልቅ ሚና እንዲጫወቱ ማድረግ ያስፈልጋል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በዚህም አረንጓዴ፣ ውብና ምቹ ኢትዮጵያን በመገንባት ለትውልዱ እናስረክባለን ሲሉ ተናግረዋል።