አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀረሪ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በአንድ ጀምበር 600 ሚሊየን ችግኞች የመትከል መርሐግብር እየተካሄደ ይገኛል፡፡
ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የመንግስት እና ግል ተቋማት ሰራተኞች፣ የፀጥታ ተቋማት፣ የሀይማኖት አባቶች፣ ወጣቶች፣ ተማሪዎች፣ መምህራን ጨምሮ አርሶ አደሮች እና የክልሉ ነዋሪዎች በንቃት እየተሳተፉ ይገኛሉ።