አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፓሪስ ፓራሊምፒክ ውድድር ላይ ለሚሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑክ ቡድን የሽኝት ስነ-ስርዓት ተካሄደ፡፡
የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ በሽኝት መርሐ-ግብሩ ባስተላለፉት መልዕክት ÷ የኢትዮጵያ ስፖርት ፖሊሲ አካል ጉዳተኞችን በስፖርቱ እኩል ተሳታፊና ተጠቃሚ መሆን እንዳለባቸው የሚያስቀምጥ በመሆኑ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
ለዚህም ማሳያ በፓሪስ በፈረንጆች 2024 በሚደረገው የፓራሊምፒክ ውድድር ኢትዮጵያን ለሚወክለው ልዑክ ቡድን አስፈላጊው ድጋፍ መደረጉን እንደገለጹ የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
በ2024 የፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር የሚሳተፉ አትሌቶችን እና ልዑካን ቡድን አባላት የሀገርና የህዝብ ኃላፊነትና አደራ ያለባችሁ መሆኑን እያሰቡ እንደ ቶክዮ 2020 ፓራሊምፒክ ውድድር በድል እንድትመለሱ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡