አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቼይ ሀይ ከተመራ የልዑካን ቡድን ጋር በኢንቨስትመንትና በልማት ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው÷በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቼይ ሀይ የተመራ የልዑካን ቡድን ተቀብዬ በኢንቨስትመንት፣ በቱሪዝም ልማት፣ በመዓድን ልማትና በአጠቃላይ የጋራ የልማት ጉዳዮች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል ብለዋል፡፡
በውይይታቸውም ÷ በጋራ በመሆን በነባር ኢንቨስትመንቶች ውስጥ ያጋጠሙ ችግሮችን መፍታት፣ ከእስካሁኑ የበለጠ ምቹ ሁኔታ መፍጠር እንዲሁም አዳዲስ ኢንቨስትመንቶችን መሳብ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መክረናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡