አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል ሆስፒታሎችን በሕክምና መሳሪያዎች ለማጠናከርና የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል አበረታች ስራ መከናወኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ ገለጹ፡፡
በክልሉ የሚገኙ ሆስፒታሎች የ2016 በጀት ዓመት ግምገማ እና የ2017 በጀት አመት ዝግጅት ላይ ያተኮረ መድረክ በጅግጅጋ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።
በመድረኩ አቶ ሙስጠፌ መሐመድ÷የክልሉ መንግስት ከለውጡ ወዲህ ሆስፒታሎችን በተለያዩ የሕክምና መሳሪያዎች ለማጠናከርና የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል ሰፊ ስራዎች ማከናወኑን ገልፀዋል።
በቀጣይም በክልሉ የሆስፒታሎችን አገልግሎት አሰጣጥ በማሳደግ ለህብረተሰቡ የተጠናከረ የህክምና አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ ማሳሰባቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡