አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሊባኖስ ታጣቂ ቡድን ሂዝቦላህ በጎላን ተራሮች ላይ የሮኬት ጥቃት መፈጸሙ ተሰምቷል፡፡
ጥቃቱ እስራኤል በቡድኑ ላይ የፈጸመችውን የአየር ጥቃት ተከትሎ የተወሰደ አጸፋዊ እርምጃ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡
የእስራኤል ጦር ትላንት ምሽት በወሰደው የአየር ጥቃት በቤካ ሸለቆ የሚገኘውን የሂዝቦላ የጦር መሳሪያ ማከማቻ ማዕከል መምታቱን አስታውቋል፡፡
ድርጊቱን ተከትሎም ሂዝቦላህ በፈጸመው የሮኬት ጥቃት በጎላን ተራሮች የሚገኙ የእስራኤል ወታደራዊ ቦታዎች ላይ ጥቃት መፈጸሙ ተገልጿል፡፡
እስራኤል የሂዝቦላህን ከፍተኛ አዛዥ በቤሩት መግደሏን ተከትሎ በታጣቂ ቡድኑ እና በእስራኤል መካከል ከፍተኛ ውጥረት መንገሱ ይታወሳል፡፡
በሂዝቦላህ እና በእስራኤል መካከል በተፈጠረው ግጭትም በሁለቱም ወገን ዘርፈ ብዙ ጉዳት እየደረሰ መሆኑን ቢቢሲ በዘገባው አስፍሯል፡፡