አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያ ባለሃብቶች በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው በሞስኮ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ፡፡
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍስሐ ይታገሱ (ዶ/ር) በሩሲያ ሞስኮ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ምክትል አምባሳደር ሮዛ የሩቅነህ ጋር በበይነ መረብ ተወያይተዋል፡፡
በዚሁ ወቅትም የሩሲያ ባለሃብቶች በግብርና ምርቶች ማቀነባበር፣ በአምራች፣ በፋርማሲዩቲካል፣ በአውቶሞቢል እና ቴክኖሎጂ ዘርፎች ኢንቨስት እንዲያደርጉ በትኩረት እንደሚሠራ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገልጸዋል፡፡
በሞስኮ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ምክትል አምባሳደር ሮዛ የሩቅነህ በበኩላቸው÷ የሩሲያ ባለሃብቶች በኢንዱስትሪ ፓርኮች ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸው ይህንም ወደ መሬት ለማውረድ እንሠራለን ብለዋል፡፡