Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

መንግሥት ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እየሠራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግሥት ሁሉን አቀፍና ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እየሠራ መሆኑን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚንስትር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

በሚኒስትሩ የተመራ ልዑክ በዓለም አቀፉ የፓርላማ ሕብረት እና በቻይና ብሔራዊ የሕዝብ ኮንግረስ አዘጋጅነት በቤጂንግ እየተካሄደ ባለው በዘላቂ ልማት ግቦች ስኬት ላይ በአተኮረው ዓለም አቀፍ ሴሚናር እየተሳተፈ ነው፡፡

በዘላቂ ልማት ግቦች የእስከ አሁን አፈፃፀም ተግዳሮትና ስኬት ላይ ከመላው ዓለም በማደግ ላይ ካሉ ሀገራት የተውጣጡ የፓርላማ አባላት በመድረኩ እየመከሩ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት የዘላቂ ልማት ግቦችን ከሀገራዊ የ10 ዓመት የልማት እቅድ ጋር አቀናጅቶ እየተገበረ እንደሚገኝ በዚሁ ወቅት ተስፋዬ በልጂጌ (ዶ/ር) መናገራቸውን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

በዚህም ሁሉን አቀፍና ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን ገልጸው÷ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም የክትትልና ቁጥጥር ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

Exit mobile version