አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፊታችን ዓርብ በአንድ ጀምበር በሚከናወነው ሀገር አቀፍ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሀ-ግብር ሁሉም የሕብረተሰብ ክፍል በንቃት እንዲሳተፍ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አሻድሊ ሀሰን ጥሪ አቀረቡ።
ነሐሴ 17 ቀን 2016 ዓ.ም ለሀገራችን ታሪክ የምንሰራበት ዕለት ነው ያሉት ርዕሰ መሥተዳድሩ÷ በሀገር አቀፍ ደረጃ 600 ሚሊየን ችግኞች ለመትከል በሚደረገው ርብርብ የክልሉ ሕዝብ የሚጠበቅበትን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በክልሉ ለሚከናወነው ችግኝ ተከላ አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁንም አስታውቀዋል፡፡