አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የልብ ቀዶ ሕክምና እና ስልጠና ለሰጡ የሕንድ እና አሜሪካ በጎ ፍቃደኞች የእውቅና እና የምስጋና መርሐ-ግብር ተካሂዷል፡፡
በመርሐ ግብሩ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ÷ኢትዮጵያ በክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ፕሮግራም የጤና ሥርዓቱን ለማሻሻል የሚያስችሉ ሥራዎች መሰራታቸውን ገልጸዋል፡፡
የበጎ ፈቃድ ቀዶ ሕክምና እና ስልጠና ለመስጠት ከሕንድ እና አሜሪካ ለመጡ ባለሞያዎችም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በጎ ፍቃደኞች ላበረከቱት አገልግሎት ያላቸውን አድናቆት ገልጸው÷በበጎ ፍቃድ አገልግሎት ለሚሳተፉ እና ድጋፍ ለሚያደርጉ አካላት አስፈላጊውን ትብብር እንደሚደረግ መናገራቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያና ህንድ ለዘመናት የዘለቀ ወዳጅነት እንዳላቸው በመርሐ ግብሩ የገለጹት በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር ሽሪል አኒል ኩማር÷ተልዕኳቸውን በስኬት ያጠናቀቁትን የሮተሪ ኢንዲያ በጎ ፍቃደኞች አመስግነዋል፡፡