አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሐ- ግብር በሸገር ከተማ አሥተዳደር ሱሉልታ ክፍል ከተማ ወሰርቢ ወረዳ ቱሉ ለሚ ዞን ለአቅመ ደካማ ቤተሰብ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡
ከድጋፉ ጎን ለጎንም የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኑረዋል፡፡
ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና ያቀረበው የወረዳው አሥተዳደር÷ እንዲህ ያሉ የበጎ ፈቃድ ተግባራት ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቋል፡፡
ድጋፉ ትምህርት ቤቶችን በማጠናከር ረገድ ቀጣይነት እንደሚኖረውም ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አረጋግጧል፡፡
በበጸሎት መንገሻ