Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኢትዮጵያ ፕሪምየር  ሊግ ዕጣ ማውጣት ሥነ-ሥርዓት ተከናወነ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2017 የውድድር ዓመት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዕጣ ማውጣት ሥነ-ሥርዓት ተከናወነ፡፡

በዚህም በመጀመሪያው ሣምንት ሀድያ ሆሳዕና ከመቐለ 70 እንደርታ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከወላይታ ድቻ፣ ስሑል ሽረ ከአዳማ ከተማ፣ አርባምንጭ ከተማ ከድሬዳዋ ከተማ፣ ሲዳማ ቡና ከሀዋሳ ከተማ ይጫወታሉ፡፡

በተጨማሪም  ቅዱስ ጊዮርጊስ  ከፋሲል ከነማ ፣ ኢትዮጵያ ቡና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ባህርዳር ከተማ ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ፣ መቻል ከወልቂጤ ከተማ በመጀመሪያው ሳምንት ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መስከረም 10 ቀን 2017 በድሬዳዋ ከተማ ስታዲየም ይጀመራል፡፡

የ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ  ባለፈው የውድድር ዓመት ከነበረው ላይ 102  ጨዋታዎች የተጨመሩበት ሲሆን÷ በዚህም በ36 ሳምንታት ውስጥ 342 ጨዋታዎች የሚደረጉ ይሆናል፡፡

በወርቅነህ ጋሻሁን

Exit mobile version