Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ የሴክተር ጉባዔ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር እንዳሻው ጣሰው በተገኙበት የክልሉ ገቢዎች ቢሮ የሴክተር ጉባዔ በቡታጅራ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

ከርዕሰ መሥተዳድሩ በተጨማሪ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ፋጤ ስርሞሎ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አንተነህ ፍቃዱ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በጉባዔው የ2016 እቅድ አፈጻጸም እና የ2017 በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ምክክር እንደሚደረግና በታክስ ሕግ ተገዢነት ላይ የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት እንደሚቀርብ ተመላክቷል፡፡

በክልሉ በ2016 በጀት ዓመት የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡም እውቅናና ሽልማት እንደሚሰጥ መገለጹን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

ክልሉ በ2017 የበጀት ዓመት ከ20 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ ወደ ሥራ መግባቱም ተገልጿል፡፡

Exit mobile version