የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያና ጃፓን ትብብራቸውን ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆናቸውን ገለጹ

By Mikias Ayele

August 19, 2024

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ሺባታ ሂሮኖሪ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም÷ በኢትዮጵያ እና ጃፓን መካከል ባሉ የሁለትዮሽ እና በባለብዙ ወገን ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡

ሀገራቱ በንግድ፣ በኢንቨስትመንትና በቀጣናዊ ሰላም ዙሪያ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡

በተጨማሪም በቶኪዮ የሚካሄደውን የቶኪዮ ዓለም አቀፍ የአፍሪካ ልማት ጉባዔ የሚኒስትሮች ስብሰባን በተመለከተ ተወያይተዋል፡፡

ጉባዔው ጃፓን ከአፍሪካ ጋር ያላትን በባለብዙ ወገን ትብብር እና አጋርነት ለማጠናከር ያለመ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡