አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገር አቀፍ ደረጃ ነሐሴ 17 ቀን 2016 ዓ.ም በአንድ ጀምበር ለሚከናወነው የችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ፡፡
በዚህም የችግኝ መትከያ ቦታ እና የሚተከሉ ችግኞችን ዓይነት ልየታ መጠናቀቁን የገለጹት በምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ማዕረግ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ ኡስማን ሱሩር÷ በ128 ቦታዎች 1 ሺህ 500 ሔክታር ላይ ችግኞች እንደሚተከሉ አስታውቀዋል፡፡
የክልሉ ደን እና አካባቢ ጥበቃ ልማት ቢሮ ኃላፊ አብርሐም መጫ በበኩላቸው በመርሐ-ግብሩ÷ ለኢንዱስትሪ ግብዓት ፣ ለግንባታ፣ ለውበት እና ለሌሎችም ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ የሚውሉ ችግኞች እንደሚተከሉ አመላክተዋል፡፡
ነሐሴ 17 ቀን 2016 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ 600 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል በተለያዩ አካባቢዎች የዝግጅት ሥራ እየተከናወነ መሆኑ ይታወቃል፡፡