ዓለምአቀፋዊ ዜና

ዩክሬን የሩሲያን ስትራቴጂካዊ ድልድይ አወደመች

By Tamrat Bishaw

August 19, 2024

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዩክሬን ወደ ሩሲያ ኩርስክ ግዛት የምታደርገውን ግስጋሴ ቀጥላ በሳምንት ውስጥ ሁለተኛውን ስትራቴጂካዊ ድልድይ ማውደሟን አስታውቃለች፡፡

የዩክሬን ወታደሮች በዝቫኖ በሚገኘው በሴይም ወንዝ ድልድይ ላይ ጥቃት ሲፈጽሙ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ይፋ አድርገዋል፡፡

በኩርስክ የተደረገው ወታደራዊ ወረራ የሩሲያን ጥቃት ለማስቆም ገለልተኛ አካባቢ መፍጠርን ያካትታል ሲሉ የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ የግስጋሴውን ዓላማ በተመለከተ ተናግረዋል፡፡

ሀገራቱ ጦርነት ከጀመሩ ወዲህ ዩክሬን ትናንት የሠረዘረችው ጥቃት ከሁለት ሣምንት ወዲህ ከፍተኛው ሲሆን÷ ባለፈው ሣምንት መጀመሪያም በግሉሽኮቮ ከተማ አቅራቢያ የሴይም ወንዝ ድልድይን ማፍረሷ ይታወሳል።

ክሬምሊን ይህን ድልድይ ወታደሮችን ለማጓጓዝ ትጠቀምበት እንደነበር ጠቅሶ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡