የሀገር ውስጥ ዜና

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የ2ኛ ዙር የትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው

By Shambel Mihret

August 18, 2024

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የ2ኛ ዙር “የትምህርት ለትውልድ” ንቅናቄ መድረክ በወራቤ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በንቅናቄ መድረኩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው፣ የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) እንዲሁም ሌሎች የሥራ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

በመድረኩ የክልሉ የትምህርት ለትውልድ 2ኛ ዙር ጠቋሚ ሰነድ፣ የቅድመ-አንደኛ ትምህርት ንቅናቄ ሰነድና የትምህርት አመራር ሪፎርም ሰነድ ቀርቧል፡፡

የቀረቡ ሰነዶችን መነሻ በማድረግም ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ይደረጋል።

“የትምህርት ለትውልድ” ንቅናቄ ለትምህርት ቤቶች መሰረተ ልማት መሻሻል ያበረከተው አስተዋፅኦን በተመለከተ ገለጻ ተደርጎ ውይይት እንደሚደረግበትም ተነግሯል።

በኤርሚያስ ቦጋለ