አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የተመራ ቡድን በምስራቅ ሐረርጌ ዞን የልማት ስራዎችን እየጎበኘ ነው፡፡
በዞኑ በክላስተር የለማ ሰብል፣ በሰው ሰራሽ ዘዴ የእንሰሳት ማዳቀል ስራ፣ በማያ ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች እንደሚጎበኙ ተገልጿል፡፡
የስራ ኃላፊዎቹ ቡድን ትናንትም በምዕራብ ሐረርጌ ዞን የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጎብኝቷል።
በጉብኝቱም በዞኑ በተለያዩ የልማት ስራዎች አበረታች ውጤት እየተመዘገበ እንደሆነ ተገልጿል።
በነጌሶ ከድር