Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሚኒስቴሩ በህፃን ሄቨን ላይ በተፈፀመው ወንጀል በተሰጠው  ውሳኔ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር  እንደሚሰራ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በህፃን ሄቨን ላይ በተፈፀመው ዘግናኝ የሆነ ኢ ሰብአዊ ወንጀል የተሰጠው ዉሳኔ አስመልክቶ ይግባኝ ለመጠየቅ የሚኬድበት አግባብ ባለመሆኑ ከባለድርሻ አካላት ጋር  እንደሚሰራ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የህፃናትን መብት በማስጠበቅ ረገድ ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ  የተለያዩ ተግባራትን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በህፃናት መብት ጥበቃ ላይ  በተለየ መልኩ  የፖሊሲ አቅጣጫዎች እንዲቀመጡና የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት  የሚፈፀሙ ጥቃቶች የሚመዘገቡበትና ተገቢ የሆነ  ሁሉን አቀፍ አገልግሎት እንዲያገኙ የህፃናት  የመረጃ አያያዝ ሰርዓት እንዲዘረጋ እና የቅንጅት ስራዎች እንዲጠናከሩ እየተደረገ መሆኑም ተመላክቷል፡፡

በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደለችውን ህፃን ሄቨን በተመለከተም በደረሰው ዘግናኝ የሆነ  ኢ-ሰብአዊ ወንጀል  ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተሰማውን ሀዘን ገልፆ ይህንን አይነት የህፃናት ጥቃት ሚኒስቴር መስሪያቤቱ በፅኑ እንደሚያወግዝ አስታውቋል፡፡

በተፈፀመው  ወንጀል ዙሪያም የተሰጠውን ዉሳኔ አስመልክቶ ይግባኝ ለመጠየቅ የሚኬድበት አግባብ ባለመሆኑ ከፍትህ አካላት እና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት እንደሚሰራ እና እንደሚከታተል አረጋግጧል፡፡

Exit mobile version