ስፓርት

በፕሪሚየርሊጉ ሊቨርፑል ኢፕስዊች ታውንን አሸነፈ

By Mikias Ayele

August 17, 2024

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየርሊግ የሁለተኛ ቀን ጅማሮ ሊቨርፑል ኢፕስዊች ታውንን 2 ለ 0 አሸነፈ፡፡

ከአዲስ አዳጊው ቡድን ከባድ ፉክክር የገጠመው የአሰልጣኝ አርኒ ሰሎት ቡድን ሊቨርፑል ከረፍት መለስ በዲያጎ ዦታ እና ሞሀመድ ሳላህ ጎሎች 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡

በጨዋታው ግብፃዊው አጥቂ ሞሃመድ ሳላህ በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያውን ጎል ሲያስቆጥር ለጎል የሚሆን ኳስ አመቻችቶ ማቀበል ችሏል፡፡

የፕሪሚየርሊጉ መርሃ ግብሮች ምሽት መካሄድ ሲጀምሩ ምሽት 11 ሰዓት ላይ አርሰናል ከዎልቭስ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው፡፡