Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ሴክቶራል ጉባዔ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ሴክቶራል ጉባዔ በቡታጅራ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር እንዳሻው ጣሰውን ጨምሮ የክልል እና በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በጉባዔው ላይ ተገኝተዋል፡፡

በጉባዔው የ2016 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2017 ጠቋሚ እቅድ ቀርቦ ምክክር እንደሚደረግ ተጠቁሟል፡፡

በክልሉ ግብረ-ኃይል የተከናወኑ ሕግ የማስከበር ሥራዎች፣ በማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያ ምክንያት ያለአግባብ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ አካላት ላይ የተወሰደ ርምጃ እና ገበያውን ለማረጋጋት የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት እንደሚቀርብም ተገልጿል፡፡

በዘርፉ የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ አካላትም እውቅና እና የማበረታቻ ሽልማት ይሰጣል ተብሏል፡፡

በተመሳሳይ የክልሉ የትምህርት ሴክተር የ2017 በጀት ዓመት እቅድ የባለ ድርሻ አካላት የውይይት መድረክ በወራቤ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ ላይ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መሥተዳድር፣ የማኅበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አንተነህ ፍቃዱ፣ የቢሮው አመራሮችና ባለሙያዎች ፣ የዞንና ልዩ ወረዳ የዘርፉ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ኤርሚያስ ቦጋለ

Exit mobile version