የሀገር ውስጥ ዜና

በአማራ ክልል የተገኘውን አንፃራዊ ሰላም ዘላቂነት ለማረጋገጥ በቅንጅትእየተሰራ መሆኑ ተመለከተ

By Amele Demsew

August 16, 2024

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል የተገኘውን አንፃራዊ ሰላም ዘላቂነት ለማረጋገጥ አመራሩ፣ የፀጥታ ኃይሉና የክልሉ ህዝብ በቅንጅት እየሰራ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ወቅታዊ የሰላም፣ የልማትና መልካም አስተዳደር ሥራዎች ያሉበትን ደረጃ ገምግመዋል።

ኅብረተሰቡ የተገኘውን አንፃራዊ ሰላም ለማወክ በማህበራዊ ሚዲያ ለሚካሄዱ የሃሰት ቅስቀሳዎች ቦታ ባለመስጠት እና ከሃሰተኛ መረጃዎች በመታቀብ ከመንግሥት ጋር በመቆም ሰላሙን ማረጋገጥ እንደሚገባው ተመላክቷል።

በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች እየተካሄዱ ያሉት ወቅታዊ የሰላም፣ የልማት እና መልካም አስተዳደር ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥሉ ዘንድ ሁሉም ባለድርሻ አካል የበኩሉን መወጣት እንዳለበት መገለጹን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በመድረኩ ዘላቂ ሰላምን ከማስፈን በተጨማሪም የሕዝብን የመልካም አሥተዳደር ጥያቄዎችን ለመፍታት እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አቅጣጫ ተቀምጧል።