የሀገር ውስጥ ዜና

ህዝቡን ተጠቃሚ ለማድረግ የአመራሩ ቁርጠኝነት ሊጠናከር ይገባል – ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድ

By Feven Bishaw

August 16, 2024

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ እና በፖለቲካዊ ጉዳዮች መላውን ህዝብ ተጠቃሚ ለማድረግ የአመራሩ ቁርጠኝነት ሊጠናከር እንደሚገባ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድ አሳሰቡ።

ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድ እና ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ጋትሏክ ሮን ከካቢኔ አባላቱ ጋር ትውውቅ አድርገዋል።

በመድረኩ ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድ፤ የካቢኔ አባላቱ ለክልሉ ሁለንተናዊ ሰላምና ልማት መረጋገጥ ግንባር ቀደም ኃላፊነት አለባቸው ብለዋል።

ህዝብን ለማገልገል የተሰጣቸውን ኃላፊነት በቅንነትና በታማኝነት በመስራት ክልሉን ወደ አዲስ ምዕራፍ ለማሻገር የካቢኔ አባላቱ ሚና ሊጠናከር እንደሚገባ ማስገንዘባቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመልክቷል።

ከትውውቅ መርሃ ግብሩ በተጨማሪ የካቢኔ አባላቱ ባካሄዱት መደበኛ ስብሰባ በቀጣይ በሚሰሩ ስራዎች በተለይም በሰላም፣ በልማትና በመልካም አስተዳደር ዙሪያ ውይይት አድርገው አቅጣጫ አስቀምጠዋል።