አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያና ሪፈራል ሆስፒታል የአዕምሮ ሕክምና መስጫ ማዕከል ተመርቋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው የምርምር ጉዳዮችና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዚዳንት ተማም አወል (ዶ/ር)÷ እያደገ የመጣውን የአዕምሮ ሕመም ከመቀነስና ከመከላከል አኳያ ማዕከሉ አይነተኛ ሚና እንደሚኖረው ተናግረዋል ።
ዩኒቨርሲተው ለአዕምሮ ሕክምና ማዕከሉ በቂ የሰው ሃይል በመመደብ አገልግሎት ከመስጠት ባሻገር በዘርፉ የተማረ የሰው ሃይልን ለማፍራት እንደሚሰራም ገልፀዋል።
ከድሬዳዋ እና አካባቢው የሚገኙ የአዕምሮ ታማሚዎች አገልግሎቱን ከዛሬ ጀምሮ ማግኘት እንደሚችሉም ተመላክቷል፡፡
በመቅደስ ደረጄ