የሀገር ውስጥ ዜና

የወደብ አማራጮችን ለማስፋት ከጎረቤት ሀገራት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

By Meseret Awoke

August 15, 2024

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የወደብ አማራጮችን ለማስፋት ከጎረቤት ሀገራት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ ባርኦ ሀሰን ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ ፥ ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ዲፕሎማሲ ንግግሮች ማድረግ መቀጠሏን ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያላትን ትብብር ማጠናከሯ መሰረተ ልማትን በመዘርጋት ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ፈተናዎችን በጋራ ለማሸነፍ ያግዛል ብለዋል፡፡

ከጎረቤት ሀገራት ጋር ሰጥቶ የመቀበል መርህ አዎንታዊ ምላሽ እየተገኘበት መሆኑንም አንስተዋል ሚኒስትር ዴኤታው፡፡

በተጨማሪም ወደቦች ላይ የሚስተዋለው ችግርን ለመቅረፍ ከጅቡቲ ጋር የጋራ ትብብር ባለስልጣን ለመመስረት ሂደቱ መጠናቀቁን ጠቅሰዋል፡፡

በአልማዝ መኮንን