አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ በጅማ ከተማ የተለያዩ የበጎ ፍቃድ ስራዎችን አስጀመሯል፡
ተቋሙ በማስጀመሪያ ፕሮግራሙ በከተማው የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ፣ የደም ልገሳ መርሀ ግብር እና የችግኝ ተከላ አከናውኗል።
በተጨማሪም በ20 ሚሊየን ብር በጀት የመዋዕለ ህፃናት እና 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለማስገንባት የመሰረት ድንጋይ ያስቀመጠ ሲሆን ደረጃቸውን የጠበቁ ስስት የአቅመ ደካማ የህብረተሰብ ክፍል የመኖሪያ ቤት ግንባታንም አስጀምሯል፡፡
የኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዋና ስራ አስፈጻሚ በሪሶ አመሎ (ዶ/ር)÷ ሎጂስቲኩ የወጪና ገቢ ንግድ ፍሰት ከማሳለጥ ባሻገር የተለያዩ የበጎ ፍቃድ ስራዎች ላይ በመሳተፍ ህብረተሰብ ተኮር ስራዎች እያከናወነ ይገኛል ብለዋል።
በዛሬው እለትም ተቋሙ በጅማ ከተማ ከ35 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የበጎ ፈቃድ ስራዎችን አከናውኗል፡፡
በወርቃፈራሁ ያለው