ዓለምአቀፋዊ ዜና

ደቡብ ኮሪያ ከሰሜን ኮሪያ ጋር ለመነጋገር ፍቃደኛ መሆኗን ገለጸች

By Tamrat Bishaw

August 15, 2024

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኮሪያው ፕሬዚዳንት ዩን ሱክ ዮል ከሰሜን ኮሪያ ጋር ያለውን ውጥረት ለማርገብና የኢኮኖሚ ትብብርን ለመቀጠል የሚያስችሉ መንገዶችን የሚያከናውን አዲስ የሥራ ቡድን ለማቋቋም ሀሳብ አቅርበዋል።

አዲሱ የሥራ ቡድንም የቀጣናውን ውጥረት ማርገብን ጨምሮ የኢኮኖሚ ትብብር፣ የሰዎች ለሰዎች እና የባሕል ልውውጥ እንዲሁም ከአየር ንብረት ለውጥ እና የአደጋ ምላሽ ጋር የተያያዙ ማንኛውንም ጉዳዮች ሊዳስስ እንደሚችል ተናግረዋል።

ፕሬዚዳንቱ አያይዘውም ፒዮንግያንግ ኒውክሌርን ለማስወገድ አንድ እርምጃ የምትወስድ ከሆነ ሀገራቸው ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብር ለመጀመር ዝግጁ መሆኗንም አመላክተዋል።

በሁለቱ ኮሪያዎች ግንኙነት መካከል ውይይት እና ትብብር ቁም ነገር ያለው መሻሻል ሊያመጡ እንደሚችሉም ዩን መናገራቸውን ዲ ደብሊው ዘግቧል።