አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በተያዘው የበጀት ዓመት አብሮነትን የሚያጠናክሩ ሥራዎች ላይ በትኩረት ይሠራል ሲሉ የባሕል እና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ አመላከቱ፡፡
የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ የሕዝብ ተወካዮች፣ የክልል እና የከተማ አሥተዳደር የሥራ ኃላፊዎች በደሴ ከተማ አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኑረዋል፡፡
በዚሁ ወቅትም ተቋማቸው ለተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍን ማድረጉን እንዲሁም ለአቅመ ደካሞች ማዕድ ማጋራቱን እና ለቤት እድሳት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉን ሚኒስትሯ ለአሚኮ ተናግረዋል፡፡
የሕዝብን አብሮነት እና አንድነት ለማጠናከር የተለያዩ ተግባራት እንደሚከናወኑ እና ለዚህም የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች የሚጠበቅባቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ጠይቀዋል፡፡