አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዋና መስሪያ ቤትን ጎብኝተዋል፡፡
ሚኒስትሩ በብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት ሲጎበኙ፥ ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡
የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ በትምህርቱ ዘርፍ ውስጥ ለተማሪዎች መታወቂያና ለ12ተኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና እንደ ዋና ልዩ መለያ በመሆን ስርዓቱን ዲጂታላይዝ ለማድረግ ዓይነተኛ ሚና እንደሚኖረውም ነው የተጠቆመው፡፡
በተጨማሪም በነበረው መግባቢያ መሠረትም ሥራዎች እየቀጠሉ መሆኑን ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ተመልክተዋል።