ቴክ

የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታን በማጎልበት የፋይናንስ አካታችነትን ለማረጋገጥ እየተሠራ መሆኑ ተመላከተ

By Shambel Mihret

August 14, 2024

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታን በማጎልበት የፋይናንስ አካታችነትን ለማረጋገጥ እየሠራች መሆኗን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

15ኛው የ “ኮኔክትድ ባንኪንግ” ጉባዔ “በዲጂታላይዜሽንና በፋይናንስ አካታችነት ኢኮኖሚን ማጎልበት” በሚል መሪ ሐሳብ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴዔታ ይሽሩን ዓለማየሁ (ዶ/ር) በመድረኩላይ የዲጂታል 2025 ስትራቴጂ እየተተገበረ መሆሁን ገልጸው÷ ስትራቴጂው የሥራ ዕድል ፈጠራን ማስፋት፣ የውጭ ምንዛሪ ግኝትን ማሳደግ እና ዘላቂ ሀገራዊ ዕድገት ለማረጋገጥ ያለመ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ጎን ለጎንም ሰው ሠራሽ አስተውሎትና የዲጂታል ዘርፎች ላይ እየተሠራ መሆኑን ገልጸው÷ ለዚህም የመሠረተ-ልማትና አስቻይ ሥርዓት የማመቻቸት ተግባራት እየተከናወኑ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በፈረንጆቹ ከ2025 እስከ 2030 ሁለተኛው የዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ እንደሚተገበርም ጠቁመዋል፡፡