Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ በአፍሪካ ድንገተኛ የህብረተሰብ ጤና አደጋ ተብሎ ታወጀ

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል(ሲዲሲ) የዝንጀሮ ፈንጣጣ ተብሎ የሚጠራውን ተላላፊ በሽታ የአህጉሪቱ ድንገተኛ የህብረተሰብ ጤና አደጋ ሲል አውጇል።

አዋጁ መንግስታት ምላሻቸውን እንዲያስተባብሩ እና ጉዳት በደረሰባቸው አካባቢዎች የህክምና አቅርቦቶችን እንዲያሳድጉ እንደሚረዳ ተጠቁሟል፡፡

የአፍሪካ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል (ሲዲሲ) ኃላፊ ጂያን ካሴያ÷ በሽታውን ለመቆጣጠር አፋጣኝ እርምጃ ካልተወሰደ ከቁጥጥር ውጪ ሊሆን እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።

በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከዓመቱ መጀመሪያ ጀምሮ ከ13 ሺህ 700 በላይ ተጠቂዎች እና 450 ህልፈት መመዝገቡ ተመላክቷል።

በሰውነት ላይ ጉዳት የሚያደርሰው ቫይረስ በቡሩንዲ፣ መካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ፣ ኬንያ እና ሩዋንዳን ጨምሮ ወደ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም መሰራጨቱን ቢቢሲ ዘግቧል።

Exit mobile version