አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጎንደር ከተማ በፌዴራል መንግሥት እየተገነቡ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን የክልሉና የከተማው ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እየጎበኙ ይገኛል፡፡
የአማራ ክልል ርዕስ መስተዳድር አረጋ ከበደ፣ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ይርጋ ሲሳይ፣ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ደብሬ የኋላን ጨምሮ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ናቸው ፕሮጀክቶቹን እየጎበኙ የሚገኙት፡፡
በዚህም የአዘዞ-አርበኞች አደባባይ የመንገድ ፕሮጀክት፣ የፋሲል አብያተ መንግስታት የቅርስ ጥገና የኮሪደር ልማት ስራዎች እየተመለከቱ ነው እንደከተማው ኮሙኒኬሽን መረጃ።