አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ምዕራፍ አጀንዳ የማሰባሰብ ሥራን አስጀመሯል፡፡
ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም በከተማው ከሚገኙ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች በአጀንዳ ማሰባሰብ ሒደት የሚሳተፋ 1 ሺህ ተወካዮችን አስመርጦ ማዘጋጀቱን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽነር አምባሳደር መሃመድ ድሪር ገልጸዋል።
አጀንዳ ማሰባሰቡ ከዛሬ ጀምሮ ለስድስት ተከታታይ ቀናት የሚቀጥል መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡
በዚህም የማህበረሰብ ተወካዮች፣ የመንግስት አካላት፣የፓርቲ ተወካዮች፣የተለያዩ ተቋማት እና ማህበራት ተወካዮች እንዲሁም ታዋቂና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች አጀንዳቸውን ያስይዛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የአስተዳደሩ ነዋሪዎች በአጀንዳ ማሰባሰብ ሒደቱ በንቃት እንዲሳተፉ ኮሚሽነሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በፈቲያ አብደላ እና እዮናዳብ አንዷለም