Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በኡጋንዳ በመሬት መንሸራተት አደጋ የ21 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኡጋንዳ ዋና ከተማ ካምፓላ የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው የመሬት መንሸራተት አደጋ እስከ አሁን የ21 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል።

በከተማዋ ኪቲዚ በተሰኘው የቆሻሻ መጣያ ሥፍራ ነዋሪዎች በተኙበት የተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ፥ በሰዎች፣ እንስሳት እና ቤቶች ላይ ጉዳት ማድረሱ ተገልጿል።

አደጋውን ተከትሎም እስከ አሁን የ21 ሰዎች ሕይወት ማለፉ እና ከ1 ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ በሰጡት መግለጫ÷ አደጋው በደረሰበት አካባቢ የሚኖሩት ሰዎችን የማስወጣት ስራ እንዲሰራ መመሪያ መስጠታቸውን ተናግረዋል።

ይህንንም ስራ ጠቅላይ ሚኒስትሯ ሮቢናህ ናባንጃ የሚያስተባብሩት መሆኑን ገልጸዋል።

የነፍስ አድን ሥራው መቀጠሉን እና እስከ አሁንም 14 ሰዎችን ጨምሮ በርካታ እንስሳትን ከሞት መታደግ መቻሉን ሬውተርስ ዘግቧል።

Exit mobile version