አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች የመዝጊያ ሥነ-ሥርዓት 80 ሺህ ተመልካቾችን በሚያስተናግደው በስታድ ደ ፍራንስ ብሔራዊ ስታዲየም ከምሽቱ 4 ሠዓት ጀምሮ ይከናወናል፡፡
የኦሊምፒክ ባንዲራም 34ኛውን የኦሊምፒክ ጨዋታዎች በፈረንጆቹ 2028 ለምታስተናግደው ሎስ አንጀለስ የውድድር አዘጋጆች የማስተላለፍ መርሐ-ግብር ይከናወናል፡፡
ፓሪስ ያስተናገደችው 33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ከሐምሌ 19 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄድ መቆየቱ ይታወቃል፡፡
በኦሊምፒኩ ኢትዮጵያ 1 የወርቅ እና ሦስት የብር ሜዳሊያዎችን በማግኘት ተሳትፎዋን አጠናቅቃለች፡፡