Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያ በሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር ውድድር የሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ መግባት አልቻለችም

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፓሪስ እየተካሄደ ባለው 33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ በሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር ውድድር የሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ መግባት አልቻለችም።

ከምሽቱ 3 ሰዓት ከ15 ላይ በተካሄደው የ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች የፍጻሜ ውድድር ኢትዮጵያን በመወከል አትሌት ድርቤ ወልተጂ እና ጉዳፍ ፀጋይ ተሳትፈዋል።

በዚህም አትሌት ድርቤ ወልተጂ አራተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን ስታጠናቅቅ፤ አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ 12ኛ ሆና ውድድሩን ጨርሳለች።

በኦሎምፒኩ ኢትዮጵያ በአትሌት ታምራት ቶላ በወንዶች ማራቶን ወርቅ እንዲሁም በ10 ሺህ ሜትር ወንዶች አትሌት በሪሁ አረጋዊ እና በ800 ሜትር ሴቶች ድጌ ዱጉማ ባመጡት ብር በአንድ ወርቅና በሁለት ብር ሜዳሊያዎች 48ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

Exit mobile version