አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ በአትሌት ታምራት ቶላ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ በማግኘቷ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ በፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ ጀግናው አትሌት ታምራት ቶላ በማራቶን ውድድር ላይ ወርቅ በማግኘት ሰንደቅ አላማችንን በድጋሚ ከፍ አድርጓል ብለዋል።
በውጤቱም መላው ኢትዮጵያውያን እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡